ቀጥታ፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ ነሀሴ 12/2020(ኢዜአ) አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን በተመለከተ ባሰራጨው ዘገባ ዙሪያ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያውያን ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ እሰራለሁ ያለው ተቋሙ በኢትዮጵያ አሁን ያለውን ፖለቲካዊ ሁኔታ እንደሚረዳ አስታውቋል።

በመሆኑም ይህን ከግንዛቤ ባላስገባ መልኩ በቅርቡ የወጣው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ በቀጣይም ገለልተኛ የሆነ እና መረጃን መሠረት ያደረገ ዘገባን ብቻ እንደሚሰራ ገልጾ፤ ከዚህ በፊት ላሰራጨው የተሳሳተ ዘገባ በቲውተር ገፁ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከዚህ በፊት በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ደርሷል ያላቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ሪፖርት ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

የወጣውን ሪፖርት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የመንግስት አካላትና ምሁራን ያሉበት ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዮን በሪፖርቱ በተጠቀሱ ቦታዎች በመሄድ አጣርቶ ምላሽ መስጠቱም አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም