በአዲስ አበባ 47 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እፅ ይዘው የተገኙ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

147

አዲስ አበባ ነሀሴ 12/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ 47 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እፅ ይዘው የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የወንጀሉ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አሮጌው ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በቁጥጥር ስር ሲውሉ 47 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፅ እጅ ከፍንጅ መያዙን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን ደረጄ ቱሉ ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በባጃጅ ጭነው በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም