በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ ቀናት በአንዳንድ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ይቋረጣል - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ ቀናት በአንዳንድ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ይቋረጣል
አዲስ አበባ፣ ነሓሴ 11/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ 3 ቀናት በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመብራት አገልግሎት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።
አገልግሎቱ የሚቋረጠው ነገ ማክሰኞ ነሐሴ 12 / 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ በአዲሱ ገበያ፣ በሰሜን ማዘጋጃ፣ በላዛሪስት ትምህርት ቤት፣ በሩፋኤል ቤተ-ክርስትያን፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም በኢምፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣቢያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡30 ድረስ ቦሌ መድሃኒዓለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በጎላጎል፣ በቺቺኒያ፣ በቦሌ ሚሊኒየም፣ በሰሚት ኮንደሚኒየም እስከ በፍየል ቤት፣ በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ በዘነበወርቅ ቶታል፣ በአለርት ሆፒታል፣ በገርጂ ዩኒቲ ኮሌጅ፣ በቦሌ ሆምስ፣ በቦሌ ሲቪል አቬሽን፣ በጎሮ አለማየሁ ህንፃ፣ በጃክሮስ፣ በተወካዮች ምክር ቤት እና አካባቢዎቻቸው፣
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ረፋዱ 9፡00 ድረስ በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በእየሩሳላም ሆቴል፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በእንቁላል ፋብሪካ እና አካባቢዎቻቸው፣
በተጨማሪም ሀሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ፡-
በኢትዮ-ፕላስቲክ፣ በየነገው ሰው ትምህርት ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በቦሌ መድሀኒያለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ እና አካባቢዎቻቸው መብራት እንደሚቋረጥ መስራቤቱ አሳዉቋል።
ተቋሙ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ደንበኘች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።