ኢትዮጵያዊ እሴት ዳግም እንዲያብብ በትብብር ሊሰራ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያዊ እሴት ዳግም እንዲያብብ በትብብር ሊሰራ ይገባል

አዲስ አበባ ነሀሴ 11/2012 (ኢዜአ) ጥንት የነበረው ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት ዳግም እንዲያብብ ሁሉም አካል በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ የኃይማኖት አባቶች አስገነዘቡ።
የኃይማኖት አባቶቹ ይህን ያሉት ባሳለፍነው ወር በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ግርግር ንብረታቸው የወደመባቸውን ወገኖች ባጽናኑበት ወቅት ነው፡፡
የኃይማኖት አባቶቹ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ተከባብሮና ተዋዶ አብሮ የሚኖር ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ግጭቶች፣ አለመግባባቶች፣ ሁከቶችና ጥቃቶች ለንጹሃን ዜጎች ሕልፈትና ለንብረት ውድመት ምክንያት እየሆኑ እንደሆነ አውስተዋል።
የተፈጸሙት ድርጊቶች አስነዋሪና ከሰብአዊነት ብሎም ከኃይማኖት የራቁና የተወገዙ ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የተፈጸሙ እንደሆነም ገልፀዋል።
''እነኚህ የጥፋት ተግባራት መደጋገማቸው ትውልዱ ላይ ያለመሥራት ውጤት ነው'' ብለው፤ የተፈጸመው ድርጊት የሰው ልጅ በራሱ ላይ ጥፋት የማወጅ ያህል እንደሚቆጠር ገልጸዋል።
ድርጊቱ አሳፋሪ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ገልጸው፤ ዳግም እንዳይከሰት ሁሉም አካል በትብብር መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ንቡረ ዕድ ኤሊያስ አብርሃ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በተከሰተው ችግር የጠፋው ንብረት የአንድ ሰው ቢመስልም የሀገር ሀብት በመሆኑ እንደሰው በማገናዘብ ለሰዎች ደህንነት ልናስብ ይገባል ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ የሚተሳሰብና የሚከበበባር ነበር አሁን ላይ የሚታየው ተግባር አሳዛኝ ነው የሚሉት ሼኽ መሀመድ ሲራጅ ኡመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የሠላምና እርቅ ዘርፍ ኃላፊ ናቸው ይህ ባህል በመጥፋቱ ሁላችንም ወደ ቀድሞው ልንመለስ ይገባል ብለዋል፡፡
የደረሰው አደጋ ልብ የሚሰብርና ከኢትዮጵያ ባህልም ሆነ ከየትኛውም የወረደ ስብእና በመሆኑ ዳግም እንደማይከሰት እምነት አለኝ የሚሉት አባ ገብርዔል ወልደሃና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምክትል ጸሐፊ ናቸው፡፡
ባለፉት አራት አስርት አመታት አባቶችን ያለማድመጥና ያለመታዘዝ ይታያል ያሉት ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን መካነ ኢየሱስቄስ ዶክተር ዋቅሹም ኢዶሣ ይሄም የሀይማኖት አባቶች ያለ ማስተማር ብቻ ባለመሆኑ ሁሉም አካል የድርሻውን ማበርከት አለበት ብለዋል፡፡
ጥንት የነበረውን ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት ዳግም እንዲያብብም መንግሥት፣ የኃይማኖት አባቶች እና ሁሉም የሚመለከተው አካል በትብብር ሊሰራ እንደሚገባም የኃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል፡፡
''የትኛውም ኃይማኖት ቢሆን ጥላቻና መገዳደልን ሳይሆን ሕዝቦች በአንድ ላይ ሆነው ያለ ልዩነት ተዋደውና ተከባብረው እንዲኖሩ ያዛል፤ ያስተምራልም'' ብለዋል።
እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር ለማስቀረት የኃይማኖት ተቋማት ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
''በኃይማኖት ውስጥ ያሉ የመከባባር፣ የመዋደድ፣ የመተጋገዝና የመተሳሰብ ትምህርቶች በወጣቱ ሊተገበሩ ይገባል'' ብለዋል፡፡
የኢትየጰያዊ እሴት እዲያድግ የሀይማኖት ተቋማትና የትምህርት ተቋማት ማስተማር አለበት የሚሉት ንቡረ ዕድ ኤሊያስ አብርሃ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ናቸው፡፡
ጉዳቱ ከሰማነው በላይ ነው ክፋትንም የትኛውም ሀይማኖት የማይደግፈው በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት የሀይማኖት አባቶች ህብረተሰቡ ጋር ወርደው ማስተማር አለባቸው የሚሉን ሼኽ መሀመድ ሲራጅ ኡመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የሠላምና እርቅ ዘርፍ ኃላፊ፡- ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኛው ወጣት በመሆኑ የሚነገረውን የሚመረምር መሆን አለበት የሚሉን አባ ገብርዔል ወልደሃና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምክትል ጸሐፊ፡-
እምነታችንንም በተግባ መዋል አለበት ብለዋል፡፡
እያንዳንዱ ቤተሰብ እግዚአብር የሰጠውን ልጅ በአንድነትና በስነምግር የሚያድጉበትን ስራ መስራት አለበት ይሄም የማህበረሰብም ሆነ የሀገር መሰረት በመሆኑ የሚሉን ቄስ ዶክተር ዋቅሹም ኢዶሣ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርሰቲያን መካነ ኢየሱስ ናቸው፡፡
ለትውልዱ በጎ በጎውን በማስተማር ሰብአዊነት የሚሰማውና ለአገርና ለሕዝቡ ተቆርቋሪ በማድረግ ቤተሰብ፣ የትምህርትና የኃይማኖት ተቋማት፣ የአገር ሽማግሌዎችና መንግሥት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።