ፖሊስ ለ3 አመታት ቤት የተቆለፈበትን ግለሰብ ህይወት ታደገ

18

ነሃሴ 9/2012 (ኢዜአ) ፖሊስ በናይጀሪያ ሰሜናዊ ካኖ ከተማ በወላጅ አባቱና በእንጀራ እናቱ ለሶስት አመታት ቤት የተቆለፈበትን ግለሰብ ህይወት ታደገ።

የ30 አመቱ አህመድ አሚኑ ሱስ ትጠቀማለህ በሚል ምክንያት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቀልፎበት ሶስት አመታትን አሳፏል።

ግለሰቡ የናይጀሪያ ፖሊስ በጎረቤቶቹና አንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት በደረሰው ጥቆማ መሰረት በቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት ባደረገው ፍተሻ ነው ሊገኘው የቻለው።

አሚኑ በደረሰበት ኢ-ሰባዊ ድርጊት ምክንያት መንቀሳቀስ እንደማይችልና በአሁኑ ሰዓትም በተሽከርካሪ ታግዞ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ያየሀገሪቱ ፖሊስ እንዳለው ግለሰቡ ላይ በተለይ ጉልበቱና አጥንቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

ይህ ወጣት እነዚህን አመታት ያለ በቂ ምግብም ሆነ ውሃ በአሰቃቂ ሁኔታ መቆየቱን በናይጀሪ የሚገኝ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ሃላፊ ሃሩና አያጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

እንደ ሃላፊው ገለጻ ጥቂት ጊዜያትን ቆይቶ ቢሆን ኖሮ ህይወቱ ሊያልፍ ይችል ነበረ።

የግለሰቡ ቤተሰቦች በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደምገኙ ተገልጿል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም