ተጨማሪ 1 ሺህ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ16 ሰዎች ሕይወትም አልፏል

72

ነሀሴ 07/2012 (ኢዜአ) ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ በተደረገው 14ሺህ 688 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 86 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 26 ሺህ 204 ደርሷል።

እንዲሁም የተጨማሪ 16 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ፤በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 479 መድረሱም ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 193 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ይገኛሉ፤ 14 ሺህ 295 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር የሕክምና ክትትል ላይ የሚገኙ ናቸው ።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 394 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 428 ደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 550 ሺህ 119 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም