አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸውን የሚመለከት ዳኛ እንዲቀየር አቤቱታ አቀረቡ

135

አዲስ አበባ ነሀሴ 4/2012(ኢዜአ) በወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ግለሰቦች ጉዳያቸውን የሚመለከት ዳኛ እንዲቀየር አቤቱታ አቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት ባለ ሰባት ገጽ አቤቱታ ጉዳዩን እየተመለከቱት ያሉት ዳኛ ገለልተኛ ናቸው ብለው እንደማያምኑ በመግለጽ ዳኛው እንዲነሱ ጠይቀዋል።

በወንጀል ጉዳይ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 የተለያዩ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ልደታ አዳራሽ ታይቷል።

ችሎቱ የቀዳሚ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት የተሰየመ ቢሆንም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ባቀረቡት አቤቱታ "ችሎቱን የሚመለከቱት ዳኛ ገለልተኛ ሆነው ጉዳያችንን ሊመለከቱ ስለማይችሉ ይነሱልን" ሲሉ አመልክተዋል።

ጉዳዩን የመረመሩት ዳኛ በበኩላቸው "ከጉዳዩ መነሳት የለብኝም" የሚል ሐሳብ አቅርበው በሰጡት ትዕዛዝ ጉዳዩ ለፍርድ ቤቱ ሬጅስትራል እንዲቀርብ አዘዋል።

ጉዳዩ በሬጅስትራሉ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ተጠርጣሪዎች በማረሚያ እንዲቆዩ በመወሰን መዝገቡ መዘጋቱን አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም