በኢትዮጵያ ተጨማሪ 552 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ15 ሰዎች ህይወትም አልፏም

58

አዲስ አበባ  ነሐሴ 01/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9 ሺህ 203 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ552 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዛሬው እለትም 388 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 415 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።

ሌሎች 174 ሰዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል።

አጠቃላይ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 21 ሺህ 452 ሲሆኑ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 11ሺህ 655 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 15 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አጠቃላይ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርን 380 አድርሶታል።

በአጠቃላይ በአገሪቱ 478 ሺህ 017 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም