አገሪቱ ከተደቀነበት አደጋ ለመጠበቅ ለወጣቱ ትውልድ የግብረገብ ትምህርት ሊሰጠው እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ

53

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2012 (ኢዜአ) አገሪቱ ከተደቀነበት የመከፋፈል አደጋ ለመጠበቅ ወጣቱ ትውልድ በሥርዓተ ትምህርቱ የግብረገብ ትምህርት ሊሰጠው እንደሚገባ የሃይማኖት ተቋማተ የበላይ ጠባቂዎቹ ጉባኤው አስገነዘበ።

የበላይ ጠባቂዎቹ ጉባኤው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባደረገበት ወቅት እንዳስገነዘቡት ከሙአለ ሕፃናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለው እርከን ትምህርቱ መሰጠት ይኖርበታል።

በዚህም የአገሪቱን ሕዝቦች የመቻቻል እሴት ማስቀጠል እንደሚቻል አመልክተዋል።

የሃይማኖት አባቶችን ያለማክበርና በተለያዩ አጀንዳዎች የመሳብ አባዜ ትውልዱን በአግባቡ ያለመታነጹ  ውጤት እንደሆነ ገልጸዋል።

በመሆኑም ወላጆች፣መንግሥትና መምህራን በጋራ በመስራት የሕዝቦችን መከባበርና አብሮ የመኖር እሴት ማስቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም