ትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው

107

አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2012 (ኢዜአ) የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ነው።

ሚኒስቴሩ ውይይቱን እያካሄደ ያለው በስሩ ካሉ 10 ተጠሪ ተቋማት ጋር ሲሆን የተቋማቱ ዝርዝር የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ነው።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በቅርቡ አጠቃላይ የትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ይፋ መሆኑን አስታውሰዋል።

ዕቅዱን ለመተግበር በተቋማት ያለውን ቁርጠኝነት ማወቅና በባለቤትነት እንዲመራ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ዕቅዱ ባለፈው አንድ ዓመት አለም አቀፍ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በባለሙያዎች መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ዕቅዱ ኢትዮጵያ አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችል በመሆኑ ለእቅዱ ትግበራና ስኬት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ውይይቱ ለ3 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የ10 ተጠሪ ተቋማት መሪ ዝርዝር ዕቅዶች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም