ቀጥታ፡

ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 26/2012 ( ኢዜአ) ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን ገለጹ።

ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ሆነው በዛሬው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል።

በተለይ በአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ድጋፋቸውን ጡሩምባ (ትላክስ) በማሰማት፣ እጃቸውን በማውለብለብና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮህ "ድምፃችን ለግድባችን" ብለዋል።

በመዲናዋ ጎዳናዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እግረኞችም "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን፣ ይህ ትውልድ የግድቡ አርበኛ ነው" በማለት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል።

በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እጃቸውን በማውለብለብ በደስታ ስሜት ታጅበው በመጮህና በማፏጨት በማድመቅ " ድምፃችን ለግድባችን" እነሆ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም