ቀጥታ፡

የግድቡ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት በስኬት መጣናቀቅ ለግንባታው የምናደርገውን አስተዋጽኦ እንድናጠናክር አነሳስቶናል--የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች

ሀምሌ 26/2012(ኢዜአ) የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ የግድቡ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት በስኬት መጣናቀቅ ለግድቡ  ቀሪ ስራ የሚያደርጉትን  አስተዋጽኦ እንዲያሳድጉ መነሳሳት እንደፈጠረባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ግድብ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  ካነጋገራቸ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል  በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት  አቶ አህመድ ሙክታር እንደገለጹት የግድቡን የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በዜና ሲሰሙ ከፍተኛ ደስታ ፈጥሮባቸዋል።

አቶ አህመድ ከዚህ በፊት ለግድቡ ግንበታ የሚውል የ5 ሺህ ብር ቦንድ መግዛታቸውን አስታውሰው   ̎በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራዬን ማሳረፌ  ደስታዬን  እጥፍ ድርብ አድርጎታል  ̎  ብለዋል ።

የዚህ ትውልድ አካል በመሆናቸውም ኩራት እንደሚሰማቸውም ነው ገልጸዋል።  

 ̎ህዳሴ ግድብ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ በተጨማሪ የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ጭምር በመሆኑ እስከ  ፍጻሜው ድረስ የማደርገውን ድጋፍ   አጠናክሬ እቀጠላለሁ̎   ሲሉም አቶ አህመድ ጠቅሰዋል።

የግድቡ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት መሳካት  ቦንድ ለመግዛት እንዳነሳሳቸውም የገለጹት ደግሞ በጫማ ማስዋብ ስራ የተሰማሩት አቶ ዮሃንስ ማሞ ናቸው።

እንደ አቶ ዮሃንስ ገለጻ የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ የፈጠረባቸው መነሳሳት ደጋግመው በ ̎8100 A̎ መልዕክት  በመላክ ድጋፍ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል።

በቀጣይም ቦንድ በመግዛት ለህዳሴ ግድብ ግንባታ በተቻላቸው አቅም የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ግድቡ ውሃ ተሞልቶ ኢትዮጵያ እንዳትጠቀም በአንዳንድ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ሲንጸባረቁ የነበሩትን የማደናቀፍ ድርጊት ሰብሮ በተያዘለት ጊዜ  የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ  ኩራት እንዲሰማኝ አድርጎኛል ያሉት ደሞ ሌላው በአልባሳት ንግድ ስራ የተሰማራው አቶ ወጅራ በረዳ  ናቸው ።

ከዚህ በፊት ሶስት ጊዜ ቦንድ መግዛታቸውን የገለጹት አቶ ወጅራ ወደ ፊትም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ  ለመጀመሪ ዙር ሃይል ለማመኝጨት የሚያስፈልገውን 4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ  ውሃ  ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም