ሲቢኤም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ ለተቸገሩ አካል ጉዳተኞች 50 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ሲቢኤም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ ለተቸገሩ አካል ጉዳተኞች 50 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አዲስ (ኢዜአ) ሐምሌ 23/ 2012 ክርሰቲያን ብላይንድ ሚሽን የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ 564 አካል ጉዳተኞች 50 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ የተደረገላቸው አካል ጉዳተኞች በቀጥታ ድጋፍ 1 ሺህ 600 ብር የሚሰጣቸው ሲሆን በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ናቸው።
የሲቢኤም ፕሮጀክት ኦፊሰር ትዕግስት ብርቅነህ እንደገለጹት፤ ዛሬ የተደረገዉ ድጋፍ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለችግር የተጋለጡ አካል ጉዳተኞችን ለመደገፍ ታስቦ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡
ሲቢኤም ከዚህ በፊት የአካል ጉዳተኞችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎች ሲያከናውን የቆየ መሆኑን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ በበኩላቸው በኮቪድ-19 የተነሳ ያጋጠመውን ጉዳት በመተባበር መወጣት እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል።
የገንዘብ ድጋፍ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ 105 አካል ጉዳተኞች ድጋፉ የተሰጠ ሲሆን በባህርዳር፣ በአዳማ እና በሃዋሳ ከተሞች የሚገኙ አካል ጉዳተኞች በቀጣይ ድጋፉ እንዲደርሳቸው የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል።