ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው።

ውይይቱ በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ  ነው።

በውይይቱ  በሰባት  አጀንዳዎች ላይ ምክክር የሚደረግ  ሲሆን፣ በቅድሚያ ግን ውይይት  የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎች ተለይተዋል።

ተወያዮቹ በቅድሚያ በአገራዊ መግባባት ላይ ውይይት ለማድረግ ተስማምተዋል።

በዚህም ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች  ተመርጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዓቢይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ባንዳዎች  ገጥመው  እንደነበር ገልጸው፤ባንዳዎቹን በመቋቋም የመጀመሪያውን ዙር የውሃ ሙሌት አሳክተናል ብለዋል።

በመንግሥትና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት በቀጣይም በአገራዊ ምርጫ ላይ አተኩሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም