ለህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ዜጎች በጋራ እንዲሰለፉ ጥሪ ቀረበ

47

አዲስ አበባ  (ኢዜአ) ሀምሌ 19/2012ዓም  ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በስኬት እንዲጠናቀቅ ዜጎች  በጋራ እንዲሰለፉ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ጥሪ አቀረቡ።

 ሚኒስትሯ እንዳሉት አገሪቱን ከድህነት የሚያወጣ እና የአፍሪካ ቀንድ አገሮችንም የሚጠቅም ነው''  ሲሉ ከኢዜአ ጋር  ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ ግድቡ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት  በመሆኑ በቀጣይም በስኬት እንዲጠናቀቅ ዜጎች  በጋራ እንዲሰለፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ግድቡ አገሪቱን ወደ ብልጽግና ምዕራፍ ለማሸጋገር ድልድይ ነው የሚሉት ሚኒስቷሯ ወጣቶች  የግንባታ ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሹ አካላት መጠቀሚያ እንዳይሆኑ  ሊጠነቀቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በየትኛውም መድረክ ለመደመጥ በኢኮኖሚ የተሻለ አቅም ያለው አገር መሆን የሚጠይቅ በመሆኑ ጠንክሮ ሰርቶ የዜጎችን ህይወት መለወጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ስራ መጠናቀቁ በዚህ ሳምንት መገለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም