የኢትዮጵ ቀይ መስቀል ማህበር ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ለሰብአዊ ድጋፍ አዋለ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵ ቀይ መስቀል ማህበር ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ለሰብአዊ ድጋፍ አዋለ
አዲስ አበባ ሐምሌ 17/2012 (ኢዜአ)የኢትዮጵ ቀይ መስቀል ማህበር ከ500
ሚሊዮን ብር በላይ ለሰብአዊ ድጋፍ ማዋሉን አስታወቀ፡፡
ማህበሩ ለኮቪድ 19 መከላከልም 128 ሚሊዮን ብር መድቦ እየተንቀሳቀሰ
ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በ2012 በጀት ዓመት ከ500 ሚሊዮን ብር
በላይ የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
የማህበሩ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ ለኢዜአ እንደገለጹት ማህበሩ ለዘላቂ
ልማት ፣ ለምግብ ዋስትና፣ የተፈናቀሉና ከስደት የተመለሱ ወገኖችን
ለማቋቋም የሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ማህበሩ በመላ አገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎቹ በተለዩ ምክንያት የተከሰቱ ግጭቶች
ተፈናቅለው ለነበሩ ዜጎች የማቋቋም ና ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡
ከስደት የተመለሱ ኢትዮጵያውያንን ተቀብሎ የሚያርፉበትን ቦታ ማመቻቸትና
ዘላቂ ድጋፍ እንዲያገኙ የማድረግ ስራዎች እንደተሰሩም ነው የተናገሩት፡፡
በአብነትም በክልሎች ለሚገኙ ከ16ሺ በላይ ዜጎች የደረቅ ራሽን ምግብ ድጋፍ
ማድረግ፤ የአምቡላንስ አገልግሎት ከ500ሺ እስከ 700ሺ ለሚሆኑ ወላድ እናቶች
መስጠቱንና በመድሃኒት መሸጫዎቹም ደግሞ ከ3.5 እስከ 5 ሚሊዮን
ለሚደርሱ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ መድኃኒት ማቅረቡም ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከ38ሺ በላይ በጎ ፈቃደኞችን
በማሰልጠን በመላ አገሪቱ ከ28 ሚሊዮን ለሚልቁ ዜጎች ግንዛቤ እየሰጠ
መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
አክለውም በአገሪቱ ኬላዎች፣ መነኻሪያዎች ፣ አየር ማረፊያዎችና በተመረጡ
ቦታዎች ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ሰዎች የወረርሽኝ ልየታ ስራ መሰራቱን
አስረድተዋል፡፡
የኬሚካል ርጭት ለ5ሺ 701ተቋማት ሲደረግ በንጽህና መጠበቂያ አቀርቦት
ከ7 ሚሊዮን በላይ እንዲሁም ለለይቶ ማቆያ የሚያገለግሉ 259 ሺ በላይ
ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ
ስራዎች መከናወናቸውን ዶክተር መሸሳ አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም ኮቪድ 19 የሚያደርሰወን ጉዳት ለመከላከል 123 ሚሊዮን ብር
በጀት መመደቡን አስረድተዋል ዋና ጸሃፊው፡፡
ከካናዳ የቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባባር 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት
ዘመናዊ የኮሮና መመርመሪያ መሳሪያ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባትም እተሰራ
መሆኑን አክለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚሹ
ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡