ቀጥታ፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ የነገውን የሀገራችንን ተስፋ ያለመለመ ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ድሎች የሚያነሳሳ ነው...ጠቅላይ አቃቤ ህግ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2012(ኢዜአ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ የነገውን የሀገራችንን ተሰፋ ያለመለመ ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ድሎች የሚያነሳሳ ነው ሲል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለጸ።

ተቋሙ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የዉሃ ሙሌት መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰማዉን ደስታ በመግለጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለኢዜአ በላከው መግለጫ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ የነገውን የሀገራችንን ተስፋ ያለመለመ ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ድሎች የሚያነሳሳ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች ባለፉት ዓመታት ለፕሮጀክቱ ስኬት ተሳትፏቸውን በተለያየ መልክ የገለፁበት እና ግንባታው ለአፍታ እንዳይገታ በቁጭት የተረባረቡበት መሆኑንም ጠቅሷል መግለጫው።

በስኬቱ ጠላቶቻችንን አንገት ያስደፋ ታሪካዊ የውሃ ሙሌት ምዕራፍ ላይ ሆነን በቀጣይም ግድቡን በመጠበቅ መሰረታዊ ዓለም አቀፍ ህግጋትን በማክበር የተፈጥሮ ፀጋችንን ፍትሃዊ በሆነ አግባብ የመጠቀም መብታችንን ሳንደራደር የሚንቀጥል ይሆናልም ብሏል።

የእኛነታችን ተምሳሌትና የህዝቦች አንድነትና ጥንካሬ እንዲሁም አልሸነፍ ባይነት የታየበት የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት እውን በመሆኑ ተቋሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ለዚህ ታሪካዊ የግድብ ስኬት በአመራር፣ በሙያ፣ በእወቀት፣ በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምስጋና አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም