የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

56

አዲስ አበባ ሐምሌ 17/2012 (ኢዜአ) የቀድሞው  የታንዛኒያ  ፕሬዚዳንት  ቤንጃሚን  ምካፓ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ ፡፡

ፕሬዚዳንት ማካፓ በ81 አመታቸው  ክትትል በሚያደርጉበት  ዳሬሰላም ሆስፒታል ህይወታቸው ማለፉን  የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

ቤንጃሚን ማካፓ ለ 10 ተከታታይ አመታት  ታንዛንያን በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ ሲሆን   የህይወታቸው ህልፈት ምክንያት  ይፋ አልሆነም ፡፡

ህልፈተ ህይወታቸውን ዜና  ተከትሎም  የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ለሰባት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን ማወጃቸውም ታውቋል፡፡

ቤንጃሚን ማካፓ የታንዛኒያ ሶስተኛው ፕሬዚዳንት ነበሩ ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም