ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 328 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ  ሀምሌ 9/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6 ሺህ 911 የላቦራቶሪ ምርመራ 328 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው። 

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ምላሽን አስመልክቶ በጋራ በሚያወጡት ዕለታዊ መግለጫ እንደተመለከተው በምርመራ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 328 ሰዎች መካከል 250 ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው።

ከጋምቤላ ክልል 27፣ ከኦሮሚያ ክልል 15፣ ከትግራይ ክልል 13፣ ከአፋር ክልል 8፣ ከድሬዳዋ ከተማ  አስተዳደር 5፣  ከሶማሌ ክልል 5 ፣   ከአማራ ክልል 1 ፣ ከቤኒሻንጉል ክልል 1 እና ከሲዳማ ክልል 3 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ሕክምና እየተከታተሉ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 837 ሲሆን ከዚህ መካከል 37 ሰዎች በጽኑ ህክምና ውስጥ ይገኛሉ።

በትናትናው ዕለት 46 ሰዎች ማገገማቸው የተጠቀሰ ሲሆን  አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 4 ሺህ 814 መድረሱ ተገልጿል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሁለት ሰዎች  ሕይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን ይህም የታወቀው በአስክሬን ላይ በተደረገ ምርመራ ነው።

እስከትናንት በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 150 መድረሱም ተነግሯል።

በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ሺህ 803 ደርሷል።

በአጠቃላይ የተደረጉ የላቦራቶሪ ምርመራዎች 309ሺህ 639 መድረሱ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም