ቀጥታ፡

ኒስክ ካፒታል የፋይናንስ ተቋሙ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልግ ተናገረ

ሀምሌ 9/2012(ኢዜአ) ዋና መቀመጫውን ዋሽንግተን በማድረግ ኬንያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ አገሮች  ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኘው ኒስክ ካፒታል (NISK Capital) ኢትዮጵያ ውስጥ ጽህፈት ቤቱን በመክፈት መስራት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

በኬኒያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ከተቋሙ ዳይሬክተር ዶክተር ጄንዳይ ፍሬዘር ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ወደ ኢትዮጵያ በሚገባበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በውይይቱ አምባሳደር መለስ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተወሰደ ካለው የኢኮኖሚ ማሸሻያ አኳያ  ኒስክ ካፒታል በኢንቨስትመንት መስክ መሰማራት አንደሚችል  ገልጸዋል።

ዶክተር  ጄንዳይ ፍሬዘር በበኩላቸው በቅድሚያ  ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከኒስክ ካፒታል እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ መነጋገር እና ወደ ስራ መግባት  መጀመር እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ለመስራት የሚያስችል ሰፊ የፋይናንስ አቅም ድርጅቱ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ኒስክ ካፒታል  በምስራቅ አፍሪካ የሚንሳቀስ የፋይናንስ ድርጅት ሲሆን በፋይናንስ ኢንቨሰትመንትና በኮርፖሬት ፋይናንስ አማካሪነት ላይ አተኩሮ ይሰራል፡፡ (በኬኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ)

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም