የአሬብ ኤምሬት የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራ ሊመለሱ ነው

51

ሰኔ 22/2012 (ኢዜአ) የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ባለስልጣናት ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች ከመጪው እሁድ ጀምሮ ወደሥራ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፍ ኒውስ አሰታውቋል።

ገልፍ ኒውስ የተባባሩት አርብ ኤሚሬት የፌዴራል ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዛሬ እንደዘገበው፤ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች በሙሉ አቅማቸው ከሐምሌ 5 ቀን 2020 ጀምሮ ሥራቸውን እንዲያከናወኑ መወሰኑን ገልጿል።

ውሳኔው የተባበሩት አረብ ኤምሬት ከድህረ ኮቪድ 19 ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠርና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የነደፈችውን እስትራቴጂ እንደሚያሳይ ባለስልጣናቱ አመልክተዋል።

በመሆኑም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው ለመመለስ ዝግጁ እንዲሆኑ ባለስልጣነቱ ትዛዝ እንደሰጡ ዘገባው ጠቁሟል።

ይሁን እንጂ የተለየ የጤና እክል የገጠመው ሠረተኛ ካለ ከሀኪም የሚያመጣው መረጃ ታይቶ ችግሩ ሊታይ እንደሚችልም ተመልክቷል።

ዱባይ ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ተመርምረው ከኮቪድ19 ነፃ የሆኑ የውጪ ሀገር ዜጎች ወደ ሀገሯ መግባት እንደሚችሉ ውሳኔ ማሰለፏ ይታወሳል።

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬት የኮቪድ19 ወረርሺኝ በዓለም ላይ መከሰቱን ተከትሎ እንቅስቃሴ ገድበው በሽታውን ከተከላከሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም