በአለም በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 10 ሚሊዮን አለፉ

78

ሰኔ 21/2012(ኢዜአ) በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሚሊዮን ማለፉ ተገለጸ።

በሌላ በኩል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሲሆን ከ5 ሚሊዮን በላይ አገግመዋል መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል።

ጣሊያን የኮሮና ቫይረስ ብርቱ ክንዱን ካሳረፈባቸው አውሮፓ ሃገራት አንዷ የነበረች ቢሆንም በአሁኑ ሰአት ግን በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ዝቅተኛ ቁጥር ማዝመዝገብዋ ነው የተነገረው፡፡

እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በሳምንቱ 44 ሺህ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቅሷል፡፡

በአሜሪካ በቫይረሱ አመካኝነት ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥርም 125 ሺህ መድረሱን ነው ዘገባው ያሳየው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም