ቡሩንዲ ከ22 ዓመታት በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች

129

ሰኔ 17/2012(ኢዜአ)ቡሩንዲ ከ22 ዓመታት በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሟ ታውቋል፡፡

ከፈረንጆቹ 1998 ወዲህ ነው አገሪቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማግኘቷ የተነገረው፡፡

አናዶሉ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃንን  ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የአገሪቱ ፓርላማ አዲስ በተመረጡት ፕሬዚደንት ኤፋሪስት ኔዳይሺሚ የቀረቡትን እጩዎች ምክትል ፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል፡፡

ምክር ቤቱ በትዊተር ገጹ በኩል ባወጣው መረጃ አልን ጉይላውሜ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ ባዞምባዛ ፕሮስፐር ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዋል፡፡

በቡሩንዲ ሕገ መንግሥት መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ደግሞ  የአገሪቱ ፕሬዚደንት የተለያዩ የኃላፊነት ተግባራት በሚወጡበት ጊዜ  የድጋፍ ተግባር ያከናውናሉ፡፡

የቀድሞው ፕሬዚደንት ፒዬር ኒኩሩዌንዝዛ በድንገት መሞታቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት እንዲደረግ ባዘዘው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ግንቦት 27 ኤፋሪስት ኔዳይሺሚ በአብላጫ ድምጽ አሸናፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም