የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋችው ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋችው ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16/2012(ኢዜአ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋችው ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉይጊ ዲማዮ ጋር በሁለትዮሽ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በነራቸው ውይይት የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንዲሁም ኮቪድ- 19ን በጋራ መግታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
እንዲሁም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ መረጃ ተለዋውጠዋል።
ጣለያን የኢትዮጵያን ሪፎርም በመደገፍ እያደረገች ላለው የልማት እርዳታም አቶ ገዱ አመስግነዋል።
ኢትዮጵያ ከጣሊየን ጋር ያላትን ሀሉን አቀፍ ግንኙነትም ይበልጥ ለማጠናከር ትስራለች ብለዋል።
በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በዓለም ላይ በጠፋው የሰው ህይወት የተሰመቸውን ሃዘን የገለጹት አቶ ገዱ ኢትዮጵያ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመግታት እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በተመከለተም ገለጻ አድርገዋል።
ወረርሽኙን ለመከላከል ከዓለም አቀፉ ማህበረስብ እና ከጣሊያን ጋር በትብብር መስራቷን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ እና ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን እያደረጉት ያለውን ውይይት በተመለከተም አቶ ገዱ ለጣሊያኑ አቻቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉይጊ ዲማዮ በበኩላቸው ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትሰራ ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ለመግታት ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል።
ጣሊያን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንበታ የሶስቱንም አገሮች ጥቅም ባማከለ መልኩ በውይይት እንዲፈታ ጣሊያን ታበረታታለችም ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ።