ለአምባሳደሮች የኢትዮጵያን የሎጀስቲክስ አሰራርን በተመለከተ ሥልጠና እየተሰጠ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለአምባሳደሮች የኢትዮጵያን የሎጀስቲክስ አሰራርን በተመለከተ ሥልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16/2012 (ኢዜአ) ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት እንዲወክሉ ለተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች የአገሪቷን የሎጀስቲክስ አሰራር በተመለከተ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሥልጠናው አምባሳደሮች ስለ አገራቸው አጠቃላይ የሎጂስቲክስ አሰራር በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ብለዋል።
አምባሳደሮቹ በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያን የሚወክሉ በመሆናቸው ብሔራዊ ጥቅምን በአግባቡ ለማስጠበቅ ይሰራሉ።
ለዚህም መሰል ሥልጠናዎችን መስጠት ወሳኝ መሆኑን አምባሳደር ብርቱካን ገልጸዋል።
የዛሬው ሥልጠና በኢትዮጵያ ማሪታይም ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን አበራ አማካኝነት በመስጠት ላይ ይገኛል።
የሥልጠናው ዋነኛ ትኩረትም የአገር አቀፍ ሎጅስቲክስ ሥርዓት፣ የሎጀስቲለክስ ፖሊሲ እና ሰማያዊ ኢኮኖሚ (Blue Economy) በሚሉ ርዕሶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ታውቋል።
ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራር ጋር በተያያዘም ከየመሥሪያ ቤቶቹ በመጡ ከፍተኛ አመራሮች ተጨማሪ ሥልጠና ይሰጣል ተብሏል።