በላሊበላ የፀሐይ ግርዶሽ ለ1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ቆይታ ነበረው

72

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14 / 2012 (ኢዜአ) በላሊበላ ከተማና አካባቢው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ለ1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ የቆየ የፀሐይ ግርዶሽ መታየቱን የከተማው የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ዛሬ ሰኔ 14፣ 2012 በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60-80 በመቶ ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ እንሚታይ ተነግሯል፡፡

በዚህም የላሊበላ ከተማ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ጥበቃና የቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ተስፋው ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማው የፀሐይ ግርዶሹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መታየት የጀመረ ከጠዋቱ 2 ሰዓት አካባቢ ግርዶሹ ለቋል።

የግርዶሹ ቆይታ ለ1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ የቆየ ነበር ያሉት ሀላፊው፤ የነበረውን ክስተት በመደነቅንና በአግራሞት የአካባቢው ህብረተሰብ በመገኘት ተመልክቶታል ብለዋል።

ይህ በዘመናት አንድ ጊዜ የሚከሰት ክስተት ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ባይከሰት ኖሮ ክስተቱ ለቱሪዝም ልማት ጠቀሜታው የጎላ እንደነበርል ሀላፊው አክለው ገልጸዋል።

በቦታው የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም