ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እየሰራች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እየሰራች ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12/2012 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ጥረት እያደረገች መሆኗን የማዕድን ነዳጅ ሚኒስቴር ገለጸ።
የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ዘርፉ ላይ ባተኮረውና የአውስትራሊያ-አፍሪካ ማዕድንና ኢነርጂ ግሩፕ ባዘጋጀው ዌቢናር ላይ እንዳስረዱት አገሪቱ ማዕድኗን የምታለማበት ዕቅድ አዘጋጅታ ወደ ሥራ ገብታለች።
የማዕድን፣ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ዕቅድ፣ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ገረመው ነጋሳ
ዕቅዱ በአነስተኛ ወጪ ሀብቱን ወደ ምርት እንደሚያስገባ አመልክተው፤በዚህም ባለሀብቶችን ለመሳብና ካፒታል ለማስገባት እንደሚቻል እምነታቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ለዘርፉ ትኩረት መሰጠቱን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል። በመርሐ ግብሩ መንግሥት ዘርፉ በተሻለ የሚንቀሳቀስበት ቅድሚያ የሚያገኝበት ማሻሻያ ማድረጉን አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱን ገልጸዋል።
በዚህም ባለፉት አምስት ወራት 106 የማዕድን ፍለጋና 110 የማዕድን ማምረት ፈቃድ መሰጠቱን አስታውቀዋል።
ታንታለምና ፖታሽን ለሚያለሙ ባለሀብቶች ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን የማይኒንግ ዊክሊ ዘገባ ይገልጻል።
በተለይ ''የቴክኖሎጂ አዲስ ሸቀጥ'' ለተባለው ታንታለም ማዕድን በመንግሥትና በግል ዘርፍ እንዲለማ ትኩረት መሰጠቱን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ፖታሽ ለማምረት ማቀዷን ገልጸው''ይህምበቅርቡ በዓለም ዋነኛ አምራች ያደርጋታል'' ብለዋል።
የሚኒስቴሩ ተወካይ በሪሁን ተመስገን መንግሥት ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እያደረገ ባለው ጥረት በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ዘርፉን የሚያሳድጉ ዕቅድ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።
ይህም በ2017 መካከለኛ ገቢ ያላት አገር ለመሆን በተያዘው ዕቅድ ከዘርፉ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የምትሆንበት ፍኖተ ካርታ እንደተሰናዳለት አስረድተዋል።
አገሪቱ በኢንዱስትሪ የሚመራና ተወዳዳሪ የሆነ የማዕድን ዘርፍ እንዲኖራት መሠረተ ልማት ለማሟላት ትኩረት እንደምትሰጥ ተወካዩ ገልጸዋል።
አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር አምስት ዋነኛ ምሶሶዎች እንዳሉት ያስረዱት ተወካዩ፤ምርታማነትን ማሳደግና ሥራ ፈጠራ ያካትታል ብለዋል።
በዚህም ለዘርፉ ትኩረት መሰጠቱን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል።
በመርሐ ግብሩ መንግሥት ዘርፉ በተሻለ የሚንቀሳቀስበትና ቅድሚያ የሚያገኝበት ማሻሻያ ማድረጉን አመልክተዋል።
.