ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ሰኔ 11/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4 ሺህ 853 የላቦራቶሪ ምርምራ 195 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ በጋራ በሚያወጡት ዕለታዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ቫይረሱ የተገኘባቸው 90 ወንድና 105 ሴት ሲሆኑ ከ 1 እስከ 85 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 3 ሺህ 954 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 144 ከአዲስ አበባ፣ 12 ከአማራ ክልል፣ 12 ከትግራይ ክልል፣ 7 ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ 7 ከአፋር ክልል፣ 4 ከሶማሊ ክልል፣ 4 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከጋምቤላ ክልል እና 2 ሰዎች ከሀረሪ ክልል ናቸው። 

በተጨማሪም በሕክምና ማዕከል ውስጥ ሕክምና ሲደረግላቸው የነበሩ 2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን መረጃው ያመለክታል።

በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 65 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ 73፣ ከኦሮሚያ ክልል 5፣ ከአማራ ክልል 5 እና ከትግራይ ክልል 2 ሰዎች በአጠቃላይ 85 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ደርሷል።

በጸና የታመሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 27 ሆኗል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 202 ሺህ 214 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም