ቀጥታ፡

ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ2 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5ሺህ 274 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

በዚህም በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3ሺህ 759 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 79 ወንድና 50 ሴት እንዲሁም የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስክ 70 አመት እንደሆነ ታውቋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 85 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 11 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 10 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ 6 ሰዎች ከአማራ ክልል ፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል እንዲሁም 4 ሰዎች ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እንደሆነ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት የ 2 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ሁሉቱም በህክምና ማዕከል ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ሰዎች ነበሩም ተብሏል።

ይህም አጠቃላይ በአገራችን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 63 ደርሷል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሟቾች የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል።

በሌላ በኩል ተጨማሪ 111 ሰዎች ( 109 ከአዲስ አበባ፣ 2 ከድሬደዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 849 መድረሱን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

በጽኑ ህክምና ክትትል የሚደረግላቸው 30 ሰዎች ናቸውም ተብሏል።

እስካሁን በአገራችን አጠቃላይ 197 ሺህ 361 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም