የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 10/2012(ኢዜአ) ምክትል ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውና የጦር ኃይሎች ጠቀላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያና ሱዳን በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሁለቱ አገራት ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በጋራ መምከራቸው ይታወሳል።
የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን መወገዳቸውን ተከትከሎ ሱዳን ይገጥማት የነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ በሰላም እንዲፈታ ኢትዮጵያ በጎ ሚና መጫወቷን ሱዳን በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል።