በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 118 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 118 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
ሰኔ 9/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5102 የላቦራቶሪ ምርምራ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 118 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
በሀገራቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 61 ደርሷል፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ በጋራ በሚያወጡት መግለጫ እንደተመላከተው በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3630 ሺህ ደርሷል።
ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 60 ወንዶችና 49 ሴቶች ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 20 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ የ45 አመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 61 ደርሷል። 32 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ1 እስከ 78 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣3 ከአማራ ክልል፣ 9 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከትግራይ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣4 ሰዎች ከደቡብ ክልል ይገኙበታል።
እንዲሁም 2 ከሀረሪ ክልል እና 3 ሰዎች ከአፋር ክልል ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በትናንትናው ዕለት 118 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 738 ደርሷል።
በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ያለባቸው 2829 ሺህ ሰዎች ናቸው።
በኢትዮጵያ እስካሁን 192 ሺህ 087 የላቦራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል።