ቀጥታ፡

የ8100 A 3ኛ ዙር ዕጣ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5/2012 (ኢዜአ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ የሚካሄደው የ8100 A 3ኛ ዙር እጣ ዛሬ ወጣ።

በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት አሸናፊው የኤስኤምኤስ ቁጥር 084492978 ሲሆን የአሸናፊው ዕጣ ኮድ ቁጥር 17618387 ሆኗል።

የዕጣው አሸናፊ ሽልማት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዘመናዊ ሃይሉክስ ፒክአፕ መኪና ነው።

የሶስተኛው ዙር በስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያው የተጀመረው በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ ሲሆን ለተጨማሪ ሶስት ወር የሚቆይ ይሆናል።

ባለፉት ሁለት ዙሮች በተካሄደ የ8100 A ገቢ ማሳባሰብ ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ሰሎሞን ተካ እንዳሉት፤ ህብረተሰቡ ለግድቡ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሶስተኛ ዙር 8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ 20 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም ጠቁመዋል።

በቀጣይም ከፍተኛ ሽልማት ያለው የ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም