ቀጥታ፡

ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደግበት ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረግ አለበት--ኢትዮጵያ

ሰኔ 5/2012(ኢዜአ) ኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተፋሰሱ አገራት አሁንም ሁሉን ተጠቃሚ በሚያደርጉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ገለጸች፡፡

የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ሱዳን ባቀረበችው ምክረ ሃሳብ ላይ የኢትዮጵያ ፣የሱዳንና የግብጽ ሚኒስትሮች እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት የግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት ና የግንባታ ሂደቱን አስመልክቶ የቪዲዮ ኮንፍረንስ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ መሪነት በተካሄደው የሶስተኛው ቀን ውይይት ላይ ኢትዮጵያ የተፋሰሱ አገራት አሁንም ሁሉን ተጠቃሚ በሚያደርጉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ገልጻለች፡፡

የሶስቱ አገራት ህዝቦችን ተጠቃሚ የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ድርድሮች ደግሞ ብቸኛ አማራጭ መሆናቸውን አጽንዖት በመስጠት፡፡

በቀጣይም የተቀየሩ ሰነዶችን ለማነጻጸርና በአገራቱ ማሃል ባሉ ልዩነቶች ዙሪያ ድርድር ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱም ተጠቁሟል፡፡

ውይይቱ ቅዳሜ በሱዳን መሪነት እንደሚቀጥልም ከውሐ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘው መግለጫ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም