ቀጥታ፡

ተጨማሪ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 5 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

በዚህም በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2ሺህ 670 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 163 ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ 1 ሰው የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑ ታውቋል።

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል 117 ወንድና 47 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስክ 92 አመት ነው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 104 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ 26 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 22 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል እና 1 ሰው ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በዛረው ዕለት ተጨማሪ 5 ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያለፈ ሲሆን 2ቱ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው፣ 3ቱ ደግሞ በሕክምና ማዕከል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ታውቋሏ።

በዚህም አጠቃላይ በአገራችን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 33 ሰዎች ( 32ቱ ከአዲስ አበባና 1 ሰው ከአማራ ክልል ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 434 መድረሱን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

እስካሁን በአገራችን አጠቃላይ 165 ሺህ 151 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም