የኢትዮጵያ የብድር ማራዘሚያ ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የብድር ማራዘሚያ ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ4/2012 (ኢዜአ) የፓሪስ ክለብ አበዳሪ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ12 አገሮች የብድር ክፍያ እንዲራዘም ወስኗል።
የክለቡ አባል አገሮች ስረዛውን የሚያደርጉት የቡድን 20 አባል አገሮች የደረሱበትን የብድር ክፍያ ማራዘሚያ ውሳኔ መሠረት መሆኑን ሮይተርስ ዜና አገልግሎት አስታውቋል።
በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ 12 አገሮች የ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ክፍያ እንዲዘገይ ተወስኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ለቡድን 20 አባል አገሮች አገራት በላኩትና በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ባሳተሙት ጽሁፍ የአፍሪካ አገሮች የበኮቪድ -19 ወረርሽኝ ችግር ላይ ስለወደቁ ዕዳ እንዲሰረዝላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።
ውሳኔው አገሮች ወረርሽኙን ለመፋለም የሚያደርጉት ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል።
የክለቡና የቡድን 20 አባል አገሮች በፈረንሳይ የገንዘብ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ቀደም ሲል ለ77 አገሮች የ 36 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ክፍያ ማራዘማቸው ይታወሳል።