አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ2/2012(ኢዜአ) አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት በድጋሚ ቃል አቀባይ ሆነው መሾማቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ አክቲንግ ቃል አቀባይ አቶ አምሳሉ ትዕዛዙ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ቃል አቀባይ ሆነው ዳግም መመደባቸውን አረጋግጠዋል።
አምባሳደር ዲና ሙፈቲ በቅርቡ በግብጽ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ እንደነበርና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ይታወቃል።
አምባሳደሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት በቃል አቀባይነት ማገልገላቸው ይታወሳል።