የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዳሴውን ግድብ አጀንዳ አድርገው በመደገፍ በኩል መነቃቃት እያሳዩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዳሴውን ግድብ አጀንዳ አድርገው በመደገፍ በኩል መነቃቃት እያሳዩ ነው
አዲስ አበባ፣ ሳኔ 2/2012(ኢዜአ) የፓርቲዎቹ ተከታዮች ለግድቡ ግንባታ በተናጠል ልዩ ልዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቢቆይም እንደ ፓርቲ ግን በተደራጀ መልኩ የተደረገ ድጋፍ አለመኖሩን ነው ያስታወሱት።
ለዚህ ደግሞ ፓርቲዎቹ በግድቡ ላይ የነበራቸው የቆየ የተዛባ የፖለቲካ አተያይ ምክንያት መሆኑን ይገልጻሉ።
የገዠውም ሆነ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት ከሕዳሴ ግድቡ ምክር ቤት አባልነት ጀምሮ በዕውቀት እንዲሁም የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮችን በማስተባበር ረገድ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አቶ ሰለሞን አልሸሸጉም።
''ከአገራዊ ለውጡ በኋላ በውጭም በውስጥም የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በግድቡ ላይ የነበራቸው አመለካከት ተቀይሯል'' ያሉት አቶ ሰለሞን፣ ይህም በአገራዊ አጀንዳ ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖርና ፓርቲዎቹ ህዝባዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረጉን ነው ያመለከቱት።
በአሁን ጊዜ ለግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ በርካታ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከቦንድ ግዠ ባለፈ በዕውቀትና በዲፕሎማሲ ሥራዎች የመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸውንም ነው የሚናገሩት።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ሙሳ አደምም በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ።
በአሁን ወቅት ግድቡ ወደ መጠናቀቅ እየተቃረበ በመሆኑ የፖለቲ ፓርቲዎችም ሆኑ ህብረተሰቡ ቀደም ሲል ሲያደርግ ከነበረው የበለጠ መደገፍ እንዳለበትም ነው ገለጹት።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ "ግድቡ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት በመሆኑ ግንባታውን በፍጥነት ማጠናቀቅ ይገባል" ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገራዊ አጀንዳዎች ላይ ያለምንም ልዩነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከአገር ውስጥና ከውጭ ዳያስፖራ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት ተሰብስቧል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከአገር ውስጥና ከዳያስፖራው የቦንድ ሽያጭና ስጦታ እንዲሁም "8100" አጭር የሞባይል መልዕክት አገልግሎትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ከ605 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል።
ከዚህ ውስጥ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በሚያዝያ ወር ብቻ የተሰበሰበ ነው።
ምክር ቤቱ በ2012 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ከተለያዩ ገቢዎች ሃብት ለማሰባሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ዕቅዱን ማሳካት አልቻለም።
ይሁንና በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።