ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ሃይል በእጥፍ ልታሳድግ ነው

67

ሰኔ 1/2012(ኢዜአ) ገልፍ 365 የተባለው ድረ ገጽ እንደዘገበው፤ ሀገሪቱ በሃይል መስመሮቿ ላይ ቴክኒካዊ ሙከራዎቿን ካጠናቀቀች በኋላ ያጋጠማትን የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት ለመፍታት ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኃይል መጠን በእጥፍ እንደምትጨምር አስታውቃለች ፡፡

የሱዳኑ የኢነርጂ እና የማዕድን ሚኒስትር አዴል ኢብራሂም በትላንትናው ዕለት እንዳስታወቁት ሱዳን ከኢትዮጵያ የምታገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ብታሳድግ በቀን ከኢትዮጵያ የምታገኘውን የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ 200 ሜጋ ዋት ያደርሰዋል ብለዋል።

ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የተከናወኑት የኤሌክትሪክ መስመር ፍተሻ አብዛኛው መጠናቀቁን ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ እስከ አሁን የተደረገው ፍተሻ በቀን ከኢትዮጵያ ከ100 እስከ 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል እንድናገኝ ያስችላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም