የመረዳጃ ማህበሩ ለአቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/2012 (ኢዜአ) የጴጥሮስ ወጳውሎስ አብሮ አደግ መረዳጃ ማህበር በዊንጌት አካባቢ ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች ከ67 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ የተሰባሰበው በጴጥሮስ ወጳውሎስ አብሮ አደግ መረዳጃ ማህበር አባላት፣ የዊንጌት አካባቢ ወጣቶች ህብረት እና በአካባቢው በሚኖሩ ባለሀብቶች ትብብር ነው።

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚኖሩ ከ98 በላይ ዜጎችም የድጋፉ ተጠቃሚ ሆነዋል።

የድጋፍ አስተባባሪዎቹ ከ67 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በመግዛት በዛሬው እለት ለግሰዋል።

በክፍለ ከተማው የወረዳ 13  ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋየ በቾ ማህበሩ ባደረገው ሰብአዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ከማህበሩ አባላት መካከል 30 የሚሆኑትም በእለቱ የደም ልገሳ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም