ቀጥታ፡

ምክትል ከንቲባው ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተሳተፉ

አዲስ አበባ ግንቦት 28/2012 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተሳተፋ።

ምክትል ከንቲባውና የሃይማኖት አባቶች በመርሐ ግብሩ በመሳተፍ በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በዚሁ ወቅትእንደተናገሩት በመርሐ ግብሩ ዜጎች ያለ ምንም ልዩነት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በበኩላቸው ዛፍ መትከል ብቻ ሳይሆን፤ለመንከባከብና ለማጽደቅም ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል።

ምክትል ከንቲባው በመርሐ ግብሩ በከተማው አስተዳደር ሰባት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

እንደ ከንቲባው ገለጻ ዘንድሮ የሚተከሉት ችግኞች የተፈጥሮ ሕግጋት እንዳይዛባ የሚያደርጉ ብቻ ሳይሆኑ፤ ፍሬያቸው የሚበላ ሕዝብን ከተፈጥሮ ጋር የሚያስታርቁ ናቸው ብለዋል።

አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ለተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም