ቀጥታ፡

ቤተክርስቲያኗ በጋምቤላ ክልል ለጎግ ወረዳ 400 ሺህ ብር ግምት ያለው ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

ጋምቤላ  ግንቦት 27 / 2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የመካነ እየሱስ የምስራቅ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ከ400 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ለጎግ ወረዳ ለገሰች።

የአኝዋሃ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ የሀብት አሰባሰቢ ግብረ ሀይል ሰብሳቢ አቶ ኡጁሉ ኝጎዎ ድጋፉን ሲረከቡ እንዳሉት የኮሮና ወርርሽኝ ሊያደረስ የሚችለውን ሁለንተናዊ ጫና  ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የሁሉም ትብብር ሊጠናከር ይገባል ።

ወረርሽኙ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ጫና መሻገር የሚቻለው ሁሉም ዜጋ እርስ በእርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህሉን ማጠናከር ሲችል መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት ወረርሽኙ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና ለመከላከል ከሚያደረገው  ጥረት በተጓዳኝ የባለድርሻ አካላት እገዛ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

 በዕለቱ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ የምስራቅ ቤተል ሲነዶስ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ሌሎች ተቋማትም ተመሳሰይ ድጋፍ እንዲያደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የምስራቅ ጋምቤላ ቤተል ሲኖዶስ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ አብጀዶ አጋኛ እንደተናገሩት ''ይህን ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻለው ሁሉም  የድርሻውን ሲወጣ ነው'' ።

ቤተ ክርስቲያኗ ወረርሽኙ ሊያደረስ የሚችለውን ማህበራዊና ኢከኖሚዊ ቀውስ ግምት ውስጥ በማስገባት ድጋፍ ማድረጓን ጠቁመው በቀጣይም ሌሎች ተመሳሳይ ድጋፎችን እንደምታደርግ ገልጸዋል።

በቤተ ክርስቲያኗ ከተለገሱት ቁሳቁሶች መካከል የንስህና መጠቢቂያ አልኮል፣ ሳይኔታይዘር፣ ሳሙና፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ይገኙበታል።

በተጨማሪም ለ82 አቅመ ደካሞች ለሁለት ወር ቀለብ የሚሆን የምግብ እህል ያካተተ ነው ብለዋል ።

በቤተ ክርስተያኗ የተለገሰው የንዕህና መጠበቂያ ግብዓትና የምግብ ፍጆታ በወረዳው በአምስት ቀበሌዎች ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ድጋፍ እንደሚውል በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም