ተጨማሪ 142 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ3 ሰዎች ህይወትም አልፏል

71

ግንቦት 26/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4120 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 142 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የሦስት ሰዎችም ሕይወት አልፏል። 

በአገሪቱ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1ሺህ 486 ደርሷል።

በምርመራው ዕድሜያቸው ከሰባት እስከ 78 ዓመት ዕድሜ ክልል ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡

ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተረጋገጠው 84 ወንድና 57 ሴቶች ሲሆኑ፣ከነዚህም 140 ኢትዮጵያውያን ናቸው። እንድ የፖርቱጋልና አንድ የጅቡቲ ዜጎች ይገኙበታል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 126 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ ሁለት ሰዎች ከአፋር ክልል፣ ሰባት ከኦሮሚያ ክልል፣ ስደስት ከአማራ ክልልና አንድ ከሶማሌ ክልል ናቸው፡፡

በበሽታው የሦስት ኢትዮጵያውያን ሕይወት አልፏል።ይህም የሟቾችን ቁጥር 17 አድርሶታል፡፡

ከበሽታው 15 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 246 ደርሷል።

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ሕክምና የሚገኙት ሰዎች 1ሺህ 219  ናቸው።

በጽኑ ህክምና ክፍል ለስድስት ሰዎች ክትትል እየተደረገ መሆኑንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም