ቀጥታ፡

በሐረር አዱ የዱቄት ፋብሪካ 100 ኩንታል ዱቄት ሰጠ

ሐረር/ ኢዜአ/ ግንቦት 25 / 2012 በሐረር ከተማ የአዱ የዱቄት ፋብሪካ የኮሮና ቫይረስ ለችግር ለተዳረጉ ዜጎች የሚውል 100 ኩንታል የምግብ ዱቄት ለክልሉ መንግስት አስረከበ። 

የፋብሪካው ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ አደመ መኮንን ድጋፉን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የኮሮና መከላከል ግብረ ሃይል ሰብሳቢ ለአቶ ኦርዲን በድሪ አስረክበዋል።

በድጋፍ የተሰጠው ዱቄት 220 ሺህ ብር ግምት ያለው ሲሆን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለችግር ለተጋለጡ አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች እንደሚከፋፈል አቶ አደመ ተናግረዋል ።


ቀደም ብሎም ፋብሪካው ሐማሬሳ በተባለው መንደር ለሚገኙ አቅመ ደካሞች 60 ኩንታል ዱቄት መስጠቱን አስታውሰው ድጋፉ ለወደፊቱም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ኃይል ሰብሳቢ  አቶ ኦርዲን በድሪ ፋብሪካው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፉ ችግረኛ ወገኖች ምግብ ፍለጋ ከቤት ወጥተው ሲንከራተቱ ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ በመከላከል ረገድ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል ።

በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ገቢ ማሰባሰብና ሐብት ማፈላለግ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም በበኩላቸው እስከ አሁን ድረስ በዓይነትና በገንዘብ 10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሃብት ማሰባሰብ እንደተቻለ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም