ቀጥታ፡

በዚህ ዓመት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) በተያዘው ዓመት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በሚያዚያ ወር ብቻ 79 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡም ታውቋል።

ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ እንዳስታወቀው ለግድቡ ግንባታ በያዝነው ዓመት እስካሁን ድረስ  605 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።

ገንዘቡ የተሰበሰበው በ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብርና በቦንድ ሽያጭ ሣምንት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም ገልጸዋል።

በመሆኑም በሚያዚያ ወር ብቻ 79 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ነው የተናገሩት።

በተያዘው ዕቅድ መሠረት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ታስቦ ነበር።

ይሁንና በወቅታዊው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረግ ባለመቻሉ ለገቢ ማሰባሰቡ እንቅፋት በመሆኑ 605 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ እስካሁን 13 ነጥብ 54 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አሁናዊ አፈጻጸም 73 ነጥብ 7 በመቶ መድረሱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም