በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ለኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማእከል ተዘጋጀ

65

ሁመራ፣ ግንቦት 23 /2012 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ አዲስ የኮሮና ህክምና ማእከል መዘጋጀቱ ተገለጸ።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማእከል ያደረገው ዝግጅት በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በዶክተር ጸጋይ በሪሁና በዞኑ የጤና ባለሙያዎች ተጎብኝቷል ።

ዝግጅቱ በዞኑ የሚታየው የህክምና ማእከላት እጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍታት እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ምክትል የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል ።

የህክምና ማእከሉን የማዘጋጀትና በቁሳቁስ የማጠናከር ኃላፊነቱን ወስዶ የሰራው የካህሳይ አበራ ሪፈራል ሆስፒታል ነው ።

የሆስፒታሉ አስተባባሪ አቶ ሃይለማርያም አለሙ እንደገለፁት በሰቲት ሁመራ ከተማ የተከፈተው አዲሱ የህክምና ማዕከል ከ100 በላይ ሕሙማን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም አለው ።

ከ150 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገለት የህክምና ማዕከሉ በአንድ ሳምንት መደራጀቱ ውስጥ የሚደነቅ ነው ሲሉ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የስራ ኃላፊዎች ተናግረዋል ።

 የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ጸጋይ እንዳሉት ስርጭቱን ለመከላከል እስከ ቀበሌ ድረስ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተረባረበ ይገኛል ።

አካባቢው ከሱዳን ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት አቶ ዳንኤል ቁጥጥሩንና የመከላከል ስራውን ለማጠናከር በአራት ቀናት ውስት ተጨማሪ የለይቶ ማቆያ ማእከላት መከፈታቸውን አስረድተዋል ።

በዞኑ በአሁኑ ጊዜ የለይቶ ማቆያ ማእከላት ብዛት 29 መድረሱን ከዞኑ ጤና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም