የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ክልል የልማት እንቅስቃሴዎችን እየጎበኘ ነው

81

ግንቦት 22/2012( ኢዜአ) የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ክልል የጉራጌና ስልጤ ዞኖች የግብርና ልማት እንቅስቃሴዎችን እየጎበኘ ነው።

በፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም የተመራው የአመራሮቹ ቡድን በአሁኑ ወቅት በቡታጅራ የችግኝ ማባዣ ማዕከል ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ነው።

በቀጣይ በሁለቱ ዞኖች እየተካሄደ ያለውን የበልግ እርሻ እንቅስቃሴ እንደሚመለከቱ የደቡብ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ኃይለማሪያም ገልጸዋል።

የኩታ ገጠም እርሻና  የችግኝ ልማት  ምርጥ ተሞክሮና በኮሮና መከላከል ላይ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚመለከቱም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም