ኮይካ የኢትዮጵያ ቢሮ ግምቱ ከ345 ሺህ ብር በላይ የሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

61

 አዲስ  አበባ  ግንቦት 21/2012 (ኢዜአ) የኮሪያ ዓለም ዓቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የኢትዮጵያ ቢሮ ግምቱ 345 ሺህ 850 ብር የሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ቢሮው የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የምግብ ሸቀጥና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር እና ለአሰላ ከተማ አስተዳደር አበርክቷል።

ኮይካ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ ሳኒታይዘር፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ የእጅ ጓንት፣ በእግር በመጫን እጅ ማስታጠቢያ፣ ጤፍ፣ ዘይት፣ ሽሮና በርበሬ ድጋፍ አድርጓል።

ለዚህም 345 ሺህ 850 ብር ወጪ ማድረጉን ገልጿል።

ኮይካ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ድጋፍ ለተለያዩ ተቋማት ማበርከቱን አስታውሶ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም