ሕዝቡ የሕዳሴውን ግድብ ለማጠናቀቅ በአንድነት እንዲቆም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠየቀ

58

አዲስ አበባ ግንቦት 18/2012 (ኢዜአ) መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ በአንድነት እንዲቆም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠየቀ።

የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎችና አባላት የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር፣ በቀለም፣ በሃይማኖት፣ በብሔርና በፖለቲካ አቋም ሳይለያይ  ግንባታውን ለማጠናቀቅ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

መንግሥትም ከተፋሱስ አገራት ጋር የሚያደርገውን ድርድር በሰላማዊ መንገድ በመቀጠል ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎች አሳስበዋል።

የሃይማኖት አባቶቹ ግድቡ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የልማትና የዕድገት ተስፋ መሆኑን አስታውሰው መንግሥት የሚያደርገውን ድርድር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም