የዓለም ጤና ድርጅት የፀረ ወባ መድሃኒትን ለኮሮናቫይረስ ለመጠቀም የሚያደርገውን ሙከራ ለጊዜው አቆመ

95

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18/2012 (ኢዜአ) የዓለም ጤና ድርጅት በዓም አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 መድሃኒት ለማግኘት ሲጠቀምበት የነበረውን የፀረ ወባ መድሃኒት ( ሃይድሮክሲክሎሮክዊን ) ለጊዜው ማቋረጡን አስታወቀ።

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአምስት ቀን በፊት በታተመው ላንሰት የሕክምና መጽሔት ላይ የወጣውን የጥናት ሪፖርት መሰረት አድርጎ ነው ተብሏል።

በዚህ ጥናት መሰረት መድሃኒቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ሞት ያፋጥናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመግለጫቸው ወቅት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "የከፍተኛ አመራሮቹ ቡድን አባላቱ የሃይድሮክሲክሎሮክዊን ሙከራ ደህንነቱ ዳግም በደህንነት ቁጥጥር ቦርዱ እስኪመረመር ድረስ ለጊዜው እንዲቋረጥ ወስነዋል" ብለዋል።

ሌሎቹ የምርምር ስራዎች ግን መቀጠላቸውን በዘገባው ሰፍሯል።

ሃይድሮክሲክሎሮክዊን በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና ሌሎች መሪዎች ለኮሮናቫይረስ ሕሙማን ቢሰጥ በፍጥነት እንዲያገግሙ ያደርጋል በሚል ሲወደስ ቆይቶ እንደነበር መረጃው አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም