በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ዙሪያ የታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚረዳ መመሪያ ቁጥር 4 ተዘጋጀ

61

አዲስ አበባ  ግንቦት  17/2012 (ኢዜአ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ዙሪያ የታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚረዳ መመሪያ ቁጥር 4 መዘጋጀቱ ተገለጸ።

መመሪያው ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባና ከክልል ከተወጠጡ ህግ አስከባሪዎች ጋር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጸጻጸም ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወጥ በሆነ መልኩ እየተተገበረ እንዳልሆነም ተጠቁሟል።

ይህንን ክፍተት ለማረም የሚያስችል መመሪያ ቁጥር 4 መዘጋጀቱም ነው የተነገረው።

መመሪያው በመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት እንዲሁም የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ላይ ማሻሻያ እንዳካተተ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም